Loading…

ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስ/ማ በ2018 በጀት አመት 19ኛ ዙር 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሄደ።

May 05, 2026

በጠቅላላ ጉባኤው ላይም የተለያዩ የብድር ጣሪያ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፡፡
መረሀ ግብሩ የተደራሽ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አልማዝ ኦልጂራ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረዋል ፡፡
በማስከተልም በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን የህብረት ስራ ማህበራት ኦዲተር ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ አሳሳሽ በቀለ የተደራሽን 2017 በጀት ዓመት ኦዲት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ባለሙያዋ አያይዘውም የተደራሽን ትርፋማነት አንስተዋል፡፡
የተደራሽ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አልማዝ የስራ አመራር ኮሚቴ ሪፖርት እንዲሁም አቶ ፍቃዱ ዲሮ የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርትን በቅደም ተከተል አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም የተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስ/ማ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈፃፃም ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርቱ እንደተመላከተው የተደራሽ አባላት ቁጥር ባሳለፍነው በጀት አመት ከነበረበት 11,041 አባላት እጥፍ በሚባል ደረጃ በማደግ ዛሬ ላይ ከ21ሺ በላይ አባላት ማፍራት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
በብድር ስርጭት በኩል ከፍተኛ እድገት የታየ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት ለ862 የማህበሩ አባላት ወደ773 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ብድር መስጠት ተችሏል።
ተደራሽ ያለውን ጠቅላላ ካፒታል በ2017 ከነበረበት 421,587,934.56 ወደ 1ቢሊየን ብር ማሳደግ መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮቾ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ዋና ስራ አስኪያጅ በሆኑት አቶ አለማየሁ ታመነ ምላሽተሰቶባቸዋል።
በጉባኤው መጨረሻ የተለያዩ የብድር ጣራ ማሻሻያዎች የተደረጉ ሲሆን ከነዚህ መካከል ከዚህ በፊት እስከ 3 ሚሊየን የነበረውን የመኪና ብድር ጣሪያ ወደ 6ሚሊየን ማሳደግ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በፊት 5ሚሊየን የነበረውን የቤት ብድር ጣሪያ ወደ 10ሚሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል፡፡ በመጨረሻም አቶ አለማየሁ ታመነ የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ጠቅላላ ጉባኤው ተጠናቋል።

Tederash Assistant

Always Online