Loading…

የተደራሽ እሩጫ ከሜሪጆይ ጋር ለኩላሊት ጤና

May 24, 2026



የተደራሽ እሩጫ ከሜሪጆይ ጋራ
ተደራሽ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ በዛሬው እለት ሜሪጆይ ኢትዮጵያ በኩላሊት ጤና እና ህክምና ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር እና እያስገነባቸው ላሉት የህክምና ማእከላት ገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሆን ባዘጋጀው የጎዳና ላይ እሩጫ ስፖንሰር በመሆን ጭምር ተሳትፏል፡፡
የተደራሽ የቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች በቦታው በመገኘት ሩጫውን አካሂደዋል ፡፡ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ወደኀላ የማይለው ተደራሽ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ በኩል ላደረገው አስተዋፆ ምስጋና ቀርቦለታል፡፡ ኩላሊት ጤና፤ ሂወት ተስፋ በሚል መሪቃል በተካሄደው በዚህ እሩጫ ላይ የሜሪጆይ ኢትዮጵያ በስራች የሆኑት ሲስተር ዘቢደርን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አንጋፋ አርቲስቶች ተገኝተዋል፡፡

Tederash Assistant

Always Online